አባይ ሚዲያ ሰኔ 16፤2012

ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ “የሰላምና ጸጥታ መደፍረስ ቢያጋጥም በዛቻና ጠብአጫሪ በሆነ ተግባር የተጠመደችው ግብጽ ኃላፊነቱን እንደምትወስድ” የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል ግብጽ በቅርቡ ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት በጻፈችው ደብዳቤ ግድቡ ለአለምአቀፍ ሰላምና ጸጥታ መደፍረስ ምክንያት እንዳይሆን ተመድ ጣልቃ መግባት እንደሚያስፈልገው ገልጻ ነበር፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ገዱ ግብጽ ”‘በሀሰት የህዳሴው ግድብ ለአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ስጋት ነው’ በማለት ለጸጥታው ምክርቤት የላከችው ደብዳቤ ትክክል ባለመሆኑ ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ መገደዳቸውን” ጠቅሰዋል ኢትዮጵያ እስካሁን በቅን መንፍስ እየተደራደች ነው፤በዚህም ምክንያት መሻሻል መጥቷል ያሉት ሚኒስትሩ ነገርግን የግብጽ በቅኝ ገዥዎች ጊዜ የተፈረመውንና ኢትዮጵያ ያልሳተፈችበትን ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን መፈለግ ድርድሩ በፍጥነት እንዳይቋጭ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡

አቶ ገዱ በጻፉት ደብዳቤ ግብጽ ኢትዮጵያ “ብቸኛ እርምጃ” ልትወስድ ነው የሚል ጫፍ የነካ ግብዝነት እያሳየች ነው፤”የብቻ እርምጃ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ውስጥ የለም” ብለዋል ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ በግድቡ ዙሪያ የሶስትዮሽ ድርድር እያካሄዱ ባለበት ወቅት ግብጽ ተመድ የጸጥታ ምክርቤት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቋ ግራ እንዳጋባቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ምክርቤቱ “ግብጽ ሀቅን ኣዛብታ በቀረበችበት ደብዳቤ አይሳሳትም ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ያሉት ሚኒስትሩ ግብጽ “በናይል ላይ ፍትሀዊ ያልሆነ የቅኝ ግዛት ጊዜ የነበረን ፍላጎት ለማረጋገጥ” የምታደርገውን ጥረት ተመድ ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቃለች ተመድ በበኩሉ ሶስቱ ሀገራት በግድቡ ዙሪያ በመካከላቸው ያለውን የጎላ ልዩነት እንዲፈቱ አሳስቧል፡፡

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፋን ጃሪክ ሀገራቱ ከአመታት በፊት በሱዳን ካርቱም በተፈራረሙት “የመርሆች ስምምነት” መሰረት ችግሩን እንዲፈቱ አሳስበዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን በኩል ኢትዮጵያን እጎዳለሁ የሚል ካለ ጸቡ ከእኛ ጋር ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ምክትል አምባሳደር ዴቪድ ደንግ ተናግረዋል፡፡

“ግብጽ በደቡብ ሱዳን ወታደሮችን እያሰለጠነች ነው” የሚሉ ዘገባዎች ባለፉት ሳምንታት ወጥተው እንደነበር ይታወሳል ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት ም/ል አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ብቻ ሳትሆን ሁሉም ነገራችን ናት ብለዋል “የትኛውም አካል ኢትዮጵያን በደቡብ ሱዳን በኩል ሊያጠቃ እንደማይችል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ማረጋገጡንም ነው የገለጹት አምባሳደር ዴቪድ ደንግ አዲስ አበባም ሆነ ካይሮ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት መሆናቸውን አንስተው ከሰሞኑ የሕዳሴ ግድብን ድርድር በሚመለከት ግብጽ ጉዳዩን አፍሪካ ህብረትን አልፎ  ወደ ተባበሩት መንግስታት መውሰድ አግባብ አይደለም ነው ያሉት፡፡