አባይ ሚዲያ ዜና – ሀምሌ 15፣ 2012

የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ደረጃ የውሀ ሙሌት መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በትዊተር ገጹ ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ ባለፉት 2 ሳምንታት የዘነበው ከባድ ዝናብ የግድቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሙሌት ዕውን ሆኗል ብሏል።
ውሃው ግድቡን አልፎ መፍሰስ ጀምሯልም ብሏል መግለጫው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፣74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዝ የሚጠበቅ ሲሆን፣አሁን ባለው የግድቡ ግንባታ ደረጃ የሚጠራቀመው የውሃ መጠን 4.3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ገደማ እንደሚሆን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተነግሯል።